ኢትዮጵያ ከቻይና በምጣኔ ሀብት ልምድን መቅሰም እንደሚገባት ተጠቆመ
አርትስ 19/02/2011
ዥንዋ ዋቢ ያደረጋቸው ኢትዮጵያዊ ምሁር ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ እንዳሉት ቻይና 700 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት አውጥታለች፤ ከ1978 (እ.አ.አ) ጀምሮ አሳታፊና ስልታዊ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ መከተሏ ደግሞ ትልቅ ሚና ተጫውቶላታል፡፡
ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ እንደተናገሩት የቻይና የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ ለ40 ዓመታት በፈጣንና ቀጣይነት ያለው የምጣኔ ሀብት ዕድገት ውስጥ እንድትቆይከማስቻሉም በላይ የኤስያ አህጉር ምጣኔ ሀብት ሞተር አድርጓታል፡፡
ኢትዮጵያ ከቻይና የቀጠናው የምጣኔ ሀብት መሪነት ልምድንም መቅሰም እንደሚገባት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ቻይና በኤስያየመሠረተ ልማት ባንክ እና ብሪክስ (አዳጊ የምጣኔ ሀብት መሪ ሀገራት ጥምረት ማለትም ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድና ቻይና ያሉበት ቡድን) መሪበመሆን እንዲሁም አንድ ቀበቶ አንድ መንገድን በማስተዋወቅና በመምራት እየሄደችበት ያለውን አግባብ ኢትዮጵያ እንድትማርበትም ዶር. ቆስጠንጢኖስ ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በግንቦት 2017 (እ.አ.አ) የእስያ የመሠረተ ልማት ባንክ አባል ሀገር በመሆን ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ ይህም ለጀመረችው ተስፋንያዘለ የልማት ጉዞ ከብሪክስ ባንክ እና ከሌሎችም ድጋፍ እንደሚያስገኝላት ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና በአፍሪካ ሕብረት በከፍተኛ አማካሪነት ያገለገሉ ኢትዮጵያዊምሁር ናቸው፡፡