loading
የጉምሩክ ኮሚሽን በሁለት ሳምንት ውስጥ ተቋቁሞ ወደ ስራ ይገባል ተባለ

የጉምሩክ ኮሚሽን በሁለት ሳምንት ውስጥ ተቋቁሞ ወደ ስራ ይገባል ተባለ

ይህንን ያሉት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ናቸዉ፡፡

ወይዘሮ አዳነች እንደገለፁት እርሳቸው የሚመሩት ሚኒስቴር የቀጣይ ሁለት ሳምንታት ቀዳሚ ተግባር ይህንኑ ኮሚሽን ማቋቋም ነው።

በአሁኑ ወቅት የጉምሩክ ኮሚሽኑን ስልጣንና ተግባር የሚወስነው ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን ያነሱት ሚኒስትሯ፥ ረቂቅ ደንቡ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ሃላፊ ይመደብለታል ብለዋል።

የሀገሪቱ የገቢ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ መሻሻሎች የሚታይበት ቢሆንም ከብዙ ኢኮኖሚያዊ መለኪያዎች አንጻር ግን ገና ብዙ የሚጠበቅበት ነውም ብለዋል ሚንስትሯ።ዘገባው የፋና ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *