loading
የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎችን ቁጥር ከ20 ወደ 10 ዝቅ አደረገ

የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎችን ቁጥር ከ20 ወደ 10 ዝቅ አደረገ

አርትስ 27/02/2011

 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘሬ ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባው 20 የነበሩት የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ወደ 10 ዝቅ የተደረጉ መሆኑን ተገልጿል።

 የቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀትን ለመወሰን የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ሃሳቡ ላይ ከተወያየ በኋላ  ነው ውሳኔውን ያፀደቀው፡፡

እንደ አዲስ በተደራጁት በእያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ በስራቸው ከ2 እስከ 4 ንዑስ ኮሚቴዎች እንደሚደራጁ ተገልጿል።

በዚህም መሰረትም 10ሩ ቋሚ ኮሚቴዎች፦

  1. የህግ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  2. የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  3. የሰው ሃብት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  4. የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራ ዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  5. የተፈጥሮ ሃብት፣መስኖ እና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  6. የከተማ ልማት፣ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  7. የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  8. የገቢዎች፣በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
  9. የግብርና፣ አርብቶ አደር እና አከባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና
  10. የውጭግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ናቸው፡፡

የእያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ  አጠቃላይ የአባላት ብዛትም ከ20 እስከ 45 የሚደርስ ነው ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *