loading
የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባዔ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸዉ ግጭቶች እንዳይከሰቱ እየሰራሁ ነዉ አለ

አርትስ 28/02/2011

እስካሁን በኢትዮጵያ የተከሰቱ ግጭቶች ሃይማኖታዊ መሰረት እነደሌለው ተቋሙ እንደሚረዳና፤ሀይማኖቶች የግጭት መንስኤ እንዳይሆኑ የበለጠ ለመስራት መዘጋጀቱንም  ገልጽዋል፡

የጉባኤዉ ዋና ፀሃፊ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ ለአርትስ በአለማችን መጠነኛ የሚባሉ የሰለም ዕጦቶች ሀገር እንድትፈርስ እስከማድረግ ደርሰዋልና፤ ሰላም ሲደፈርስ ይችላል የሚል አካል ሊኖር አይገባም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሙሉ ሰላሟ ተጠብቆ የቆየችው ለጥቂት ጊዜ ነው ያሉት መጋቢ ዘሪሁን ፤አሁን ላይ አሳሳቢ የሆኑ ስጋቶችና የሰላም መደፍረስ በዚሁ ከቀጠለ የኢትዮጵያ ቀጣይ ሰላም እንደሚያሳስብ ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት እስካሁን በሰራው ስራ ብዙ ምዕመናንን ተደራሽ አድርጓል የሚጠበቅበትንም ተወጥቷል ያሉ ሲሆን ፤የህግ የበላይነት አለመከበሩና መንግስት መውሰድ ያለበትን እርምጃ በጊዜው አለመውሰዱ ችግሮች እንዲበራከቱ ምክንያት እንደሆነም ነግረውናል፡፡

ጉባኤዉ ጊዜያው ቀውሶችን በመፍታት ዘላቂ ሰላምንና አብሮነትን ለማጠናከር የሃይማኖት መሪዎች እና የማህበረሰብ ሚና በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትናየማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ዉይይት ያካሄደ ሲሆን፤ ተወያዮቹ  የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠበቅባቸውን በበቂ ሁኔታ ሰርተዋል ለማለት ይከብዳል ፤ችግሮች ሲኖሩ ብቻ ሳይሆን ፤ችግር ሳይከሰት ቀድሞ መገመትና እንዳይከሰት ማድረግ አለባቸዉ ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *