loading
በኢትዮጵያ ሰዉ ሰራሽና ተፈጥሮ አመጣሽ ችግር ሳቢያ የአረጋዉያን አኗኗር ፈተና ላይ እየወደቀ ነዉ

አርትስ 28/02/2011

 

ዛሬ በኢትዮጵያ ለ27ኛና በአለም ለ28ኛ  ግዜ በተከበረዉ  የአረጋዉያን ቀን ላይ የኢፌዴሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደተናገሩት አረጋዉያን አሁን ያለንን ቁሳዊና መንፈሳዊ ሃብት ካለፈዉ ትዉልድ ተረክበዉ ፤የራሳቸዉንም ጨምረዉ ዛሬ ያደረሱን ቢሆንም የሚገባቸዉን ክብር አላገኙም ብለዋል፡፡

አሁንም በተለያዩ ሰዉ ሰራሽና ተፈጥሮ አመጣሽ ችግር ሳቢያ የአረጋዉያን አኗኗር ፈተና ላይ እየወደቀ በመሆኑ ባለመታከት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡

ከዚህም ሌላ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች እየተከሰቱ ያሉ የጥፋት ድርጊቶች እንዲታረሙና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያላቸዉን እምቅ እዉቀትና ጥበብ በመጠቀም ያለመታከት እንዲሰሩ ዶ/ር ኤርጎጌ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአሉ “ቀደምት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾችን በመዘከር የኢትዮጵያ አረጋዉያንን ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጥ “በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ዉሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *