loading
የተቆላ የኢትዮጵያ ቡና የሚያቀርቡ ድርጅቶች ለሽልማት ታጩ

አርትስ 29/02/2011

 “ጉድ ፉድ አዋርድስ” ለተሰኘው የአሜሪካ ሽልማት ዕጩ የሆኑት የተቆላ የኢትዮጵያ ቡና የሚያቀርቡ ድርጅቶች 25 ናቸው።

አሜሪካ ውስጥ በየአመቱ በሚካሄደው በዚሁ የሽልማት ፕሮግራም ላይ እጩ የሆኑት ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች የታወቁት የ2019 የዘጠነኛው ዙር ሽልማት እጩዎች  ዝርዝር ይፋ በተደረገበት ወቅት ነው።

እንደ ደይሊ ኮፊ ዘገባ በ2019ኙ ውድድር ለመጨረሻው ዙር ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል 25ቱ የኢትዮጲያን ቡና የሚያቀርቡ ሲሆን ቀሪዎቹ 5 ተወዳዳሪዎች ከኮስታሪካ፣ ከኮሎምቢያ ከጓቲማላ፣ ከፓናማ እና ከኬኒያ መሆናቸውተውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና በዚህ ውድድር ላይ ለዕጩነት ሲቀርብም ሆነ ሽልማት ሲወስድ  የመጀመሪያው እንዳልሆነ በዘገባው ተገልጿል።

በ2018 በተደረገው የ“ጉድ ፉድ አዋርድስ” በቡና አምራችነት ዘርፍ እጩ ሆነው ከቀረቡት 27 ድርጅቶች ውስጥ 26ቱ የኢትዮጵያን ቡና የሚያቀርቡ ድርጅቶች  ነበሩ ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *