loading
አልቃኢዳና ዳኢሽ ሊዋሃዱ እንደሚችሉ ሩሲያ ስጋቷን ገለፀች

አርትስ 29/02/2011

 

የሩሲያው የደህንነት ተቋም ዳይሬክተር አሌክሳንደር ቦርቲንኮቭ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች ውህደት ፈጥረው ለመንቀሳቀስ እያሰቡ ስለመሆናቸው ፍንጮችን አግኝተናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ቦርቲንኮቭ ይህን ያሉት ሞስኮ ውስጥ በተካሄደው ለደህንነት ኤጀንሲዎች እና ለህግ አስከባሪዎች በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ነው፡፡

ሩሲያና አሜሪካ በየፊናቸው ባደረጉት ዘመቻ ዳኢሽ ሶሪያ ውስጥ እንዳያንሰራራ ተደርጎ ተመትቷል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ሆኖም ግን ቡድኑ ከአልቃኢዳ ጋር በመዋሀድ እንደገና ሀይሉን ለማጠናከር እና ሁለቱ ሃይሎች በተደራጀ መንገድ ለመምጣት እየተዘጋጁ እንደሆነም ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

ሁለቱ ድርጅች ለመዋሀድ ከሚያስችሏቸው መስፈርቶች መካከል በዋናነት አንድ ዓይነት ርእዮተ ዓለም መያዛቸው ሲሆን ተመሳሳይ የሰው ሀይል አመላመልና አደረጃጀት ያላቸው መሆኑም ተጠቃሽ ነው፣እንደ ሩሲያ ባልስልጣናት ገለጻ፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *