loading
የሰለጠኑ የኦነግ አባላት የኦሮሚያ ፖሊስን ሊቀላቀሉ ነው

የሰለጠኑ የኦነግ አባላት የኦሮሚያ ፖሊስን ሊቀላቀሉ ነው

አርትስ 03/ 03/2011

  የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦነግ አመራሮች ያደረጉትን ስምምነት መሰረት በማድረግ ወደ ሃገር ገብተው ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 1 ሺ154 የኦነግ ጦር አባላት  እንደ የፍላጎታቸው ወደ ስራ ሊሰማሩ ነው።

የኦሮሚያ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ እንዳሳወቀው፤  ስልጠና ሲወስዱ ከነበሩት የኦነግ ጦር አባላት ውስጥ 700ዎቹ በራሳቸው ፍላጎት የኦሮሚያን ፖሊስ እንቀላቀላለን በማለታቸው ግንዛቤ እንዲያገኙ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ እንዲገቡ ተድርገዋል።

የአጭር ጊዜ ስልጠና በመውሰድም የኦሮሚያን ፖሊስ የሚቀላቀሉ ይሆናል።

የቀሩትም እንደየፍላጎታቸው በግል ስራ፣ በመንግስት ስራ እና የኦነግ ፖለቲካ አባል በመሆን ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *