loading
በግብፅ የሚገኙ የቱርክ ትምህርት ቤቶች ቅሬታ እየቀረበባቸው ነው

አርትስ 04/04/2011

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፃዊው የህግ ጠበቃ ሳሚር ሳብሪ ቅሬታቸውን ይዘው ወደ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ለመሄድ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡

ምክንያቸው ደግሞ እነዚህ ትምህርት ቤቶች የግብፅን የትምህርት ካሪኩለም በሚቃረን  መልኩ እያስተማሩ ነው የሚል ነው፡፡

ለአብነት ያህልም በግብፅ መንግስት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን የሙስሊም ወንድማማቾችን አጀንዳ በግልፅ ያራምዳሉ፤ ለተማሪዎቻቸውም ይሰብካሉ የሚል ክስ ያቀርባሉ ጠበቃው፡፡

በካይሮ፣ በአሌክሳንደሪያ እና በቤኒ ሱይፍ የሚገኙት እነዚህ ትምርት ቤቶች ሌላው ችግራቸው አረብኛ ተናጋሪ መምህራንን አለመቅጠራቸው መሆኑንም ሳብሪ አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡

አሁን አሁን የትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎች በማህበራዊ ድረ ገፆቻቸው የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን የሚጠቀምበትን አርማ ሲያጋሩ መመልከት የተለመደ ሆኗል ያሉት ጠበቃው ይህም በትምህርት ቤቶቹ ቢበረታቱ ነው ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *