loading
የትግራይ ክልል በመንግስት እየተወሰደ ያለው እርምጃ የህግ የበላይነትን ባከበረ መንገድ እንዲተገበር ጥሪ አቀረበ

አርትስ 05/03/2011

ይህን ያለው የክልሉ መንግስት ትላንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

በመግለጫው አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃም  የህግ የበላይነትን ባከበረ መንገድ እንዲተገበር ጥሪ አቅርቧል፡፡

መግለጫው የትግራይ ህዝብ ፍትህን ለማስፈን ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈሉን አስታውሶ ማናቸውም ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዳይፈፀም ጥንቃቄ ሊደረግይገባል ብሏል፡፡  የትግራይ ህዝብም እንዲህ ያሉ ጥቃቶችን  በኃላፊነት እንዲታገል ጥሪ አቅርቧል።

እየተወሰደ ያለው እርምጃም እርቅንና ይቅርታን መሰረት ተደርጎ የተጀመረውን ጥረት ወደኋላ የሚመልስ እንዳይሆን  የህግ የበላይነትን ሳይሸራረፍ እንዲፈፀም የክልሉ መንግስትያሳስባል ይላል መግለጫዉ።

በቅርቡ በተካሄዱት የኢህአዴግ መድረኮች ላይም  የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የሙስና ተግባራት ማስተማሪያ ይሆኑ ዘንድ ህግንና ስርዓትን በተከተለ ፤ ብሄርን መሰረት ባላደረገ መንገድ ተጠያቂ እንዲያደርግ ከመግባባት ላይ መደረሱን መግለጫው አስታዉሷል፡፡

እየተወሰደ ባለው እርምጃ የማጣራት ሂደቱ በግልፅነትና ከማንኛውም ኃይል ተፅእኖና ውጪ እንዲሆን፤ ለዚህም  የክልሉ መንግስት እንደሚታገል እና በእርምጃው ከሚሳተፉ የዴሞክራሲ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልፀል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *