loading
ማይክፔንስ ትራምፕ ከኪም ጋር ዳግም ሲገናኙ የቀድሞውን ስህተት አይደግሙትም አሉ

አርትስ 06/03/2011

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2019 ከሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን ጋር የመገናኘት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ከአሁን በፊት የተፈጸሙ ስህተቶች እንዳይደገሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል ብለዋል ፔንስ፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው  የሁለቱ ሀገራ መሪዎች ባለፈው ሰኔ ወር የተካሄደውን የሲንጋፖሩን ስብሰባ ውጤት ለመገምገምና የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቅነሳ ላይ ለመወያያት ሁለተኛውን ቀጠሮ ይዘዋል፡

ሁለቱ መሪዎች በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ላይ ይገናኛሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ያሉት ፔንስ መቸ እና የት የሚለው ግን በሂደት የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል፡፡

ፔንስ ከአሁን ቀደም የተሰሩ ስህተቶች ያሉት ላለፉት ዓመታት በቀድሞዎቹ መሪዎች ብዙ ቃልኪዳኖች ተገብተው፣ ማዕቀቦች እንዲነሱ ተደርገው እስካሁን ድረስ የተገቡ ውሎች አለመፈፀማቸው እንደሆነ አብራርተዋል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *