loading
የካፋ ዞን ምክር ቤት የክልልነት ጥያቄን አጸደቀ

አርትስ 06/03/2011

የካፋ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ጉባዔ የካፋ ዞን የክልልነት ጥያቄን በሙሉ ድምፅ አጸድቋል፡፡

ዞኑ በተለይ ሰሞኑን ከቡና መገኛነት ጋር በተገናኘ በተፈጠረ ውዝግብ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የነበረ ሲሆን፣ለሳምንት ያክል በተካሄደ ሰላማዊ ሠልፍ ከተላለፉ መፈክሮች መካከል የክልልነት ጥያቄ አንዱ ነበር፡፡

በዚህም ምክንያት፣ የዞኑ ምክር ቤት ጉባዔውን በማድረግ ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ ማጽደቁ ታውቋል፡፡

በዞኑ መቀመጫ ቦንጋ ከተማ ወጣቶች ከፍተኛ የደስታ ሠልፎች እያደረጉ እንዳሉ እማኞች ከአካባቢው ለሪፖርተርገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ በርካታ የክልሉ ዞኖችየክልልነት ጥያቄ እየተስተዋለባቸው ሲሆን፣ በዞን ምክር ቤቶች ደረጃም በአጀንዳነት ተይዞ ውይይት የተደረገባቸውዞኖች አሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *