loading
ምክር ቤቱ የአቶ ተስፋዬ ዳባን እና ወ/ሮ ለምለም ሀድጎን ሹመት አፀደቀ

ምክር ቤቱ የአቶ ተስፋዬ ዳባን እና ወ/ሮ ለምለም ሀድጎን ሹመት አፀደቀ

አርትስ 13/03/2011

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ያልተሟሉ የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መናብርት ሹመት ለማፅደቅ የቀርበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል፡፡

በዚህም አቶ ተስፋዬ ዳባ ለውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት እንዲሁም ለገቢዎች ፋይናንስ እና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ወ/ሮ ለምለም ሀድጎ አቅርቦ አፀድቋል፡፡

የሁለቱ ቋሚ ሰብሳቢ ምደባም በአንድ ድምፀ ታቅቦ፤ በአብላጫ ድምፅ የምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 11/2011 በመሆን ፀድቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ምክር ቤቱ በአፈ-ጉባኤው በተጠራ 1ኛ ልዩ ስብሰባ የ8 ቋሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት ምደባን በተመለከተ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡

በአፈ- ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አቅራቢነት ለገቢዎች ፣ በጀትና ፋይናንስ የተከበሩ አቶ አጽብሃ አረጋዊን እንዲሁም ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ደግሞ አቶ ሞቱማ መቃሳን በእጩ የቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበርነት ቢያቀርቡም ምክር ቤቱ በአብላጫ ተቃውሞ ውሳኔውን ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *