loading
በኢትዮጵያ ያለጊዜያቸው ለሚወለዱ ህፃናት የሚዉል የህክምና ቁሳቁስ በ24.5 ሚሊዮን ዶላር ተገዛ

አርትስ 14/03/2011

በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ዛሬ በኢትዮጵያ ለ5ኛ ጊዜ የጨቅላ ህፃናት ቀን ተከብሯል፡፡

በዝግጅቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማንን ጨምሮ የዩኒሴፍ ተወካይና ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ያለጊዜያቸዉ ለሚወለዱ ህፃናት ልዩ የህክምና ክትትል መስጫ  የተገዙት የህክምና መሳሪያዎች በሃገሪቱ በሚገኙ 80 ሆስፒታሎች ተገጥመዉ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በዓመት ከ320 ሺህ በላይ ህፃናት የመውለጃ ቀናቸዉ ሳይደርስ ይወለዳሉ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ 44 በመቶ የሚሆኑት ለሞት ይዳረጋሉ፡፡

ለዚህ የሞት መጠን በዋናነት እንደምክንያት የሚነሳዉም የግንዛቤ እጥረት ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *