loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ የጋራ ተስፋችን አብሮና ተባብሮ መስራት ነው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ የጋራ ተስፋችን አብሮና ተባብሮ መስራት ነው አሉ

አርትስ 23/03/2011

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ ከምክትላቸዉ አቶ ደመቀ መኮንን እና ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር በአማራ ክልል የሚገኘውን የኩሳኤ ቀበሌ ስንዴ ማሳ ክላስተርን ከጎበኙ በኋላ ነው።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ ጉብኝት ሲያደርጉም ከአካባቢው ህብረተሰቡ ባህላዊ ስጦታዎችም ተበርክቶላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ ከስንዴ ማሳ ክላስተር ጉብኝት በማስከተል በአማራ ክልል እነዋሪ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል

በውይይቱ ላይም የስንዴ ማሳው የህብረተሰቡ ተባብሮና ጠንክሮ መስራት ውጤት መሆኑን አንስተዋል።

የጋራ ተስፋችን አብሮና ተባብሮ መስራት ነው በማለትም የአካባቢው ነዋሪዎች የጀመሩትን የአብሮነት ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ማሳሰባቸውን  ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

በማስቀጠልም ይህንን የአካባቢውን በጎ ተሞክሮ ወደ ሌሎች አጎራባች ከተማዎች ለማዛመት የከተማዋ ነዋሪዎች ቀዳሚ ሚና እንዲጫወቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *