loading
ኢራን ራሴን የመከላከል እንጂ ማንንም የማጥቃት ዕቅድ የለኝም አለች

ኢራን ራሴን የመከላከል እንጂ ማንንም የማጥቃት ዕቅድ የለኝም አለች

አርትስ 24/03/2011

ሚሳኤል በማበልፀግና ሙከራ በማድረግ ዓለም አቀፉን ህግ እየጣሰች ነው የሚል ወቀሳ  ከዋሽንግተን የሚቀርብባት ቴህራን አሁንም እቀጥልበታለሁ የሚል መልስ ሰጥታለች፡፡

ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ እንደዘገበው ኢራን ራሷን ለመከላከል የምታደርገውን የሚሳኤል የማበልፀግ ተግባር ማንም ሊያስቆማት እንደማይችል ገልፃለች፡፡

የአሜሪካን ወቀሳ አስመልክተው ምላሽ የሰጡት የኢራኑ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል አቦልፋዝል ሸክራኪ ጠላቶቻችን አደብ እንዲገዙ ነው ይህን የምናደርገው ብለዋል፡፡

የአሜሪካው የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን የኢራን ድርጊት ከትዕግስት በላይ ነው ሲሉ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ ደግሞ አሜሪካ ሌሎችን ከመክሰስ ይልቅ ራሷ ህግን ታክብር ብለዋታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *