loading
ኔታኒያሁና ፖምፒዮ በኢራን ጉዳይ ላይ መክረዋል

ኔታኒያሁና ፖምፒዮ በኢራን ጉዳይ ላይ መክረዋል

አርትስ 25/03/2011

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታናያሁና የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ብራሰልስ ላይ ተገናኝተው ነው በቴህራን የኒውክሌር በጦር መሳሪያ ዙሪያ የተወያዩት፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ሁለቱም ባለ ስልጣናት የኢራንን አዲሱን የኒውክሌር ሙከራ በጋራ አውግዘዋል፡፡

ኔታናያሁ ከፖምፒዮ ጋር በተገናኙበት ወቅት ኢራን በሶሪያ፣ በሊባኖስና በአጠቃላይ በመካከለኛው ምስራቅ  ያላትን ተፅእኖ ለመቀነስ ተግተን መስራት አለብን ብለዋቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንደሰፍን ከተፈለገ ኢራን በሶሪያ  የጦር ሰፈር ለማቋቋም የምታደርገውን እንቅስቃሴና የኒክሌር ሙከራዋን እንድታቆም ሀይ ልትባል ይገባል ሲሉም ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ጠይቀዋል፡፡

እንደኔታናያሁ ገለፃ ኢራን በሊባኖስ የሚገኙ የሂዝቦላ ታጣቂዎችን እና ሶሪያና የመን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሁቲ አማፂያንን መደገፏ የቀጠናው ቀውስ እንዲባባስ እያደረገ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *