ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቀንን ልታከብር ነው
ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቀንን ልታከብር ነው
አርትስ 25/03/2011
በቀጣይ ሰኞ የሚከበረው የሰብዓዊ መብት ቀን “universal declaration of human rights” በአለም አቀፍ ደረጃ የፀደቀበትን ቀን በማሰብ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ቀኑን ማክበር የጀመረችው ከአስራ ሁለት ዓመት በፊት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር ተናግረዋል፡፡
የሰብአዊ መብት አያያዝ ከአለም አቀፍ ህግጋቶች አንፃር ያሉበት ሁኔታም እንደሚዳሰስ በምስራቅ አፍሪካ የህጎችን መከበር ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ የበዓል አከባበር ስነ ስርዓት ሊሆን እንደሚችልም በአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቋም የአፍሪካ ተወካይ ቭዌዴ ኦባሆር ተናግረዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ለ70 ኛ ጊዜ በሚከበረው በዚህ ቀን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ ፤ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አስተዳደሮች የሚሳተፉበት የፓናል ውይይትና ዓውደ ርዕይ እንደሚኖር ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡