ናይጀሪያ የቀድሞ ሚኒስትሯ ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች
ናይጀሪያ የቀድሞ ሚኒስትሯ ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች
አርትስ 26/03/2011
የናይጀሪያ የፀረ ሙስና ተቋም የቀድሞዋ የሀገሪቱ የነዳጅ ሚኒስትር ዲዛኒ አሊሰን ማዱክ ዓለም አቀፍ የእስር ትእዛዝ እንዲወጣባቸው ጠይቋል፡፡
ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው የናይጀሪያ የፋይንስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች ኮሚሽን ተከሳሿ ለናይጀሪያ መንግስት ተላለፈው እንዲሰጡና በሀገራቸው ፍርድ ቤት እንዲዳኙ ጥያቄ አቅርቧል
አሊሰን ማዱክ በስልጣን በነበሩበት ወቅት በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ አባክነዋል ተብለው ነው በናይጀሪያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለጉት፡፡
አሁን በሚኖሩበት ለንደን ከተማ ፍርድ ቤት ቀርበው ከተጠየቁ በኋላ በዋስ የተለቀቁ ሲሆን ወደ የትኛውም ሀገር እንዳይንቀሳቀሱ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀዋል፡፡
ተጠርጣሪዋ ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ ከሆነ የጉቦ ቅሌትን ጨምሮ አምስት ክሶች ይጠብቃቸዋል ነው የተባለው፡፡