loading
በ10 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚተገበሩ የሴቶችን አቅም ለመገንባት የሚያግዙ ፕሮጀክቶች ስራ ላይ ናቸው ተባለ

በ10 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚተገበሩ የሴቶችን አቅም ለመገንባት የሚያግዙ ፕሮጀክቶች ስራ ላይ ናቸው ተባለ

አርትስ 27/03/2011

 የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የሴቶች ቢሮ ሃላፊ ሌቲ ቺዋራን አነጋግረዋል።

በውይይታቸው የመንግስታቱ ድርጅት በኢትዮጵያ በሚያደርጋቸው የስራ እንቅስቃሴዎች እና በተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ላይ መክረዋል ተብሏል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ በ10 ሚሊየን ዶላር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ሌቲ ቺዋራ የገለፁ ሲሆን በተለይ ድርጅቱ የሴቶችን አቅም ለማሳደግ የሚረዱ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ለተግባራዊነቴ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ኃላፊዋ ተናግረዋል።

ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በገኘው መረጃ ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ  የመንግስታቱ ድርጅት ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢቢሲ እንደዘገበዉ ፕሬዚዳንቷ መንግስት በቀጣይነት በዘርፉ ለመተግበር ከያዛቸው ፕሮግራሞች ጋር በማጣጣምና ውጤታማነታቸውንም በማሳደግ ለተሻለ ስራ እንዲንቀሳቀስ አሳስበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *