loading
ጀማል ካሾጊ የዓመቱ ምርጥ ሰው ተባለ

ጀማል ካሾጊ የዓመቱ ምርጥ ሰው ተባለ

አርትስ 03/04/11

ታይም መፅሄት ካሾጊን ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር የክብር እውቅናውን የሰጠው እውነትን ሲያፈላግ ዒላማ ሆኖ ህይዎቱን ያጣ ጋዜጠኛ በማለት የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰብ አድርጎ ነው።

ቢቢሲ እንደዘገበው ከካሾጊ ሌላ በዚህ ሽልማት ማይናማር ውስጥ የታሰሩ ሁለት የሮይተርስ ጋዜጠኞች፣ አሜሪካ ሜሪላንድ ውስጥ የሚታተመው ካፒታል ጋዜት እንሁዲም ማሪያ ሬሳ የተባለች ጋዜጠኛ  ተካትተውበታል፡፡

ታይም መፅሄት እንዳስታወቀው እነዚህ ጋዜጠኞች እውነት እንዳትበደል ጠበቃ ሆነው ህይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉና በስራቸው ምክንያት ከእስራት እስከ ህይወት መስዋእትነት የከፈሉ ናቸው፡፡

ለዋሽግተን ፖስት የሚፅፈውና በስደት አሜሪካ ይኖር የነበረው ጀማል ካሾጊ የሳውዲን መንግስት በድፍረት በመተቸቱ ነው ገድያ የደረሰበት በማለት በሁኔታው በርካታ ሀገራት ቅር ተሰኝተዋል፡፡

ሁለቱ የሮይተርስ ጋዜጠኞች የማይናማር መንግስት በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የፈፀመውን ግፍ በማጋለጣቸው ነው ለእስር የተዳረጉት፡፡

ማሪያ ሪሳ የተባለቸው የቀድሞ የሲን ኤን ኤን ጋዜጠኛ ደግሞ ፊሊፒንስ ውስጥ ያቋቋመችው ራፕለር የተሰኘ ድረ ገፅ በፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ትእዛዝ ተዘግቶባታል፡፡

ከዚህም አልፎ ሪሳ በታክስ ማጭበርበር እንድትከሰስና ብዙ ወካባ እንዲደርስባት ተደርጋለች ይላል ዘገባው፡፡

ካፒታል ጋዜት ጋዜጠኞችን ጨምሮ አምስት ሰራተኞቹ ባስነበበው ፅሁፍ ሳቢያ በአክራሪዎች  ተገድለውበታል፡፡

ታይም መፅሄት ይህን ሁሉ ከግምት ወስጥ በማስገባት ነው የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ተቋማት በማለት እውቅና የሰጣቸው፡፡

ጀማል ካሾጊ ከሞተ በኋላ በታይም መፅሄት የዓመቱ ምርጥ ሰው ተብሎ የተመረጠ የመጀመሪያው ሰው ሆኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *