loading
የአፍሪካ ህብረትና የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማሙ

የአፍሪካ ህብረትና የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማሙ

አርትስ 04/04/2011

የአፍሪካ ህብረትና የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የፀረሽብር ክንፎች ሽብርተኝነትን መዋጋት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ሁለት ዓመት ከፈጀ ድርድር በኋላ የተፈረመው ይህ ስምምነት ሁለቱ አካላት በዘርፉ ያላቸውን ልምድ  በመጋራት በትብብር ለመስራት ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

ይህም ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር የሽብር ስጋቶችን በተሻለ ብቃት ለመመለስ እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2001 የተቋቋመው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ሩሲያን ጨምሮ 8 የኢሲያ እና የአውሮፓ አገራት የተመሰረተ ነው፡፡

ሺንዋ እንደዘገበው የአፍሪካ ህብረት የፀረሽብር ክንፍ ደግሞ አባል አገራትን በማስተባበር ዓለም አቀፉን የፀረሽብር ትግል ለመደገፍ 2004 በአልጀርስ የተመሰረተ ተቋም ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *