የየመን ተዋጊ ሀይሎች የፈረሙትን የተኩስ አቁም ስምምነት በደቂቃዎች እድሜ አፈረሱት
የየመን ተዋጊ ሀይሎች የፈረሙትን የተኩስ አቁም ስምምነት በደቂቃዎች እድሜ አፈረሱት
አርትስ 09/04/11
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለቱን ወገኖች ብራሰልስ ላይ አገናኝቶ ለየመናዊያን የርዳታና የፍጆታ ሸቀጦች መግቢያ በሆነችው ሁዴይዳ ወደብ ውጊያ እንዲያቆሙ አስማምቷቸው ነበር፡፡
ይሁንና ስምምነቱ ተግባራዊ ከሆነ ከደቂቃዎች በኋላ በዚህች የወደብ ከተማ ግጭቱ አገርሽቶበታል ተብሏለል፡፡
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በመንግስት ወታደሮችና በሁቲ ሚሊሻዎች መካከል ዳግም በተቀቀሰው ግጭት የአካባቢው ነዋሪወች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ዓለም አቀፉ ድንበር ዘለል የሀኪሞች ቡድን በግጭቱ ሳቢያ የተጎዱ ሰዎችን የህክምና እርዳታ አድርጌላቸዋለሁ በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡
ቡድኑ አያይዞም የሲቪል ሰዎች በብዛት በሚገኙበትና በጤና ተቋማት አካባቢ የሚደረግ ጥቃት እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል፡፡
በተባበሩት መንግስታ አዳራዳሪነት ባለፈው እሁድ ብራስልስ ላይ የተፈረመው የተኩስ አቁም ስምምነት ብዙዎች ተስፋ ቢያደርጉበትም ተግባራዊ በሆነ በደቂቃዊች እድሜ መጣሱ የየመናዊያንን ተስፋ አጨልሞታል፡፡