loading
የአፍሪካ-አውሮፓ መድረክ በቪየና ተጀምሯል

የአፍሪካ-አውሮፓ መድረክ በቪየና ተጀምሯል

አርትስ 09/04/11

የአፍሪካ እና የአውሮፓ መሪዎች ስለ አህጉሮቻቸው ሊመክሩ ኦስትሪያ ቪየና ላይ የጋራ ጉባኤ አዘጋጅተዋል፡፡

የሩዋንዳው ዘ ኒው ታይምስ እንደዘገበው መድረኩ ኩባንያዎች እርስበርሳቸው እንዲሁም መንግስታት ከኩባንያዎች ጋር ሊኖራች ስለሚችለው ግንኙነት በሰፊ ይመከርበታል፡፡

በዚህ ጉባኤ  የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የንግድ ትብብርን ማጎልበት፣  የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ እና ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት የሚሉት አጀንዳዎች ለውይይት ይቀርባሉ፡፡

የአፍሪካ እና የአውሮፓ ህብረት  እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 በአቡጃው ጉባኤ የተስማሙበትን ለዘላቂ ልማትና አካታች እድገት ወጣቶች ላይ መስራት የሚለው እቅድ አተገባበር ላይም በሰፊው ይመክራሉ፡፡

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከአወሮፓ ህብረት አቻቸው ቻንስለር ሰባስቲያን ኩርዝ ጋር ጉባኤውን በጋራ ይመሩታል፡፡

በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ወደ ቦታው ካቀኑት የአፍሪካ መሪዎች መካከል ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ፣ እንዲሁም የናይጀሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት የሚ ኦሲባንጆ ይኙበታል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሺን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መዓማትና የአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት ጂያን ክላውድ ጀንከርም የጉባኤው ተሳታፊወች ናቸው፡፡

የአፍሪካ ህብረትን የፕሬዝዳንነት ቦታ በቅርቡ ከፖል ካጋሜ የሚረከቡት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አል ሲሲም በጉባኤው ለመታደም ቪየና ገብተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *