ምክር ቤቱ ብሄራዊ የሃዘን ቀን አወጀ
ምክር ቤቱ ብሄራዊ የሃዘን ቀን አወጀ
አርትስ 09/04/11
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞውን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት መለየት አስመልክቶ ብሄራዊ የሃዘን ቀን አወጇል።
ምክር ቤቱ የሀዘን ቀኑን ያወጀው ባካሄደው 4ኛ አመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ነው።
በዚህም መሰረት ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሆንዋል፡፡
በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ለአንድ ቀን የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብም ወስኗል።
በተመሳሳይ ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የሆኑ መርከቦችም በነገው የኢትዮጲያ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ያድርጉ ሲልም ምክርቤቱ አውጇል።