loading
ዶሀ ከጎረቤቶቿ ጋር ተኳርፋ ብሄራዊ ቀኗን አክብራለች

ዶሀ ከጎረቤቶቿ ጋር ተኳርፋ ብሄራዊ ቀኗን አክብራለች

አርትስ 10/04 /2011

 ኳታር ይህን ቀን የምታብረው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1878 ሸይክ ጃሲም ቢን ሞሀመድ አልታኒ የአሚርነቱን ስልጣን ከአባታቸው የተረከቡበት እና ሀገሪቱን ወደ አንድነት ያመጡበት ቀን በመሆኑ ነው፡፡

በዓሉ “ጠንክረን ከሰራን ኳታር ነፃ ሆና ትኖራለች” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በልዩ ልዩ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡

ይህ መሪ ሃሳብ የተመረጠበት ምክንያት ከዲፕሎማሲና ከንግድ ግንኙነት ላገለሏት የገልፍ  ሀገራት ራሴን ችዬ መኖር እንደምችል እወቁት የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነው ተብሏል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ኳታር ከቀድሞ ወዳጆቿ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከባህሬን፣ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችና ከግብፅ ጋር  ግንኝነቷ ተቋርጦ የብሄራዊ ቀኗን ስታከብር ሁለተኛ ጊዜዋ ነው፡፡

ሀገራቱ ኳታርን ሽብርተኞችን በገንዘብና በቁሳቁስ ትደግፋለች ብለው ከማህበራቸው ቢያስወጧትም  እሷ ግን አሁንም ክሱን አትቀበለውም፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ሀገራት ሀሳባቸውን ቀይረው ለሰላም ዝግጁ ከሆኑ ዶሀ በሯ ክፍት እንደሆነ በተደጋጋሚ ትናገራለች፡፡

የኳታሩ አሚር ሸይክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ በዶሀ ኮንፈረንስ ላይ በሉዓላዊነታችን ባንደራደርም ችግሮቻችንን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለን አቋም ግን አይቀየርም በማለት አብራርተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *