የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አስከሬን ጦር ሃይሎች ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አሸኛኘት እየተደረገለት ነው።
የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አስከሬን ጦር ሃይሎች ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አሸኛኘት እየተደረገለት ነው።
አርትስ 10/04/2011
በአሸኛኘት ስነ ስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሚኒስትሮች የተገኙ ሲሆን፥ የፕሬዝዳንቱ አስክሬን በክቡር ዘበኛ ታጅቦ ከጦር ሃይሎች ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ያመራል ተብሏል።
ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ሚሊኒየም አዳራሽ ከደረሰ በኋላም ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ፥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ሚኒስትሮች እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ የስንብት ፕሮግራም ይካሄዳል።
በስንብት ፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የስንብት ንግግር አድርገው፥ በክብር ሰረገላና በወታደራዊ ማርሽ ባንድ ታጅቦ አስክሬናቸው ወደሚያርፍበት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ያመራል።
ፋና እንደዘገበዉ በቅድስት ስላሴ ካቴድራልም ፀሎት ተደርጎና በአቡነ ዲዮስቆሪዮስ የስንብት ፕሮግራም ተከናውኖ ግብዓተ መሬት ይፈጸማል።
ለክብራቸውም መድፍ የሚተኮስ ይሆናል።