loading
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ60 ሺህ አገልግሎት ፈላጊዎችን ችግር የሚፈታ የትራንስፎርመር ግዢ ሊፈጽም ነው

አርትስ ታህሳስ 12 2011

ተቋሙ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ በቁጥር 4 ሺህ 978 የሆኑ 17 ዓይነት ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ከሁለትሃገር በቀል ድርጅቶች ጋር የግዥ ውል ፈፅሟል፡፡

ስምምነቱ  ለአንድ አመት የሚቆይ ሲሆን ግዢው ከ50 እስከ 1 ሺህ 250 ኪሎ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸውን ትራንስፎርመሮች ያካትታል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ  እንደተናገሩት የግዥ ስምምነቱ  በማህበረሰቡዘንድ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን  የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎት ለማርካት ትልቅ ጠቀሜታ አለው ።

ስምምነቱን የፈፀሙት የሁለቱ ተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው፥ ጥራት ያላቸው ትራንስፎርመሮችን በውሉ በተቀመጠውየጊዜ ሰሌዳ መሰረት አምርቶ ለማስረከብ  ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን ብለዋል።

ግዢው የህብረተሰቡን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት ወሳኝ እርምጃ ነው ተብሏል ፣ ዜናው የኢዜአ ነው።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *