የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አርትስ ስፖርት 17/04/2011
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መርሃግብር (BOXING DAY MATCHES)፡ ዛሬ ዘጠኝ ያህል ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ከቀኑ 9፡30 በክራቨን ኮቴጅ ፉልሃም ከ ወልቭስ ይጫወታሉ፤ ምሽት 12፡00 ላይ በተመሳሳይ ሰዓት በርከት ያሉ ግጥሚያዎች ሲከናወኑ፤ የሊጉ መሪ በአንፊልድ ሊቨርፑል ከ ኒውካስትል ዩናይትድ ይገናኛሉ፣ ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ወደ ኪንግ ፓወር አቅንቶ ሌስተር ሲቲን ይገጥማል፤ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር የኦልትራርድ የመጀመሪያ ጨዋታ በማንችስተር ዩናይትድ እና ሀደርስፊልድ መካከል ይከናወናል፣ በሴል ህረስት ፓርክ ክሪስታል ፓላስ ከ ካርዲፍ ሲቲ፣ በቱርፍ ሞር በርንሊ ከ ኢቨርተን፣ በዊምብሌ ደግሞ ቶተንሃም ከ በርንማውዝ ይፋለማሉ፡፡
ምሽት 2፡15 ሲል ብራይተን በአሜክስ አርሰናልን ይፈትናል፤ በቪካሬጅ ምሽት 4፡ 45 ዋትፎርድ ከ ቼልሲ ይገናኛሉ፡፡
በሊጉ ሀሙስ ምሽት 4፡45 በሴንት ሜሪ ሳውዛምፕተን ከ ዌስት ሃም ዩናይትድ ተጫውተው የሳምንቱ መርሃግብር ይጠናቀቃል፡፡
የደረጃ ሰንጠራዡን ሊቨርፑል በ48 ነጥብ ሲመራ፣ ማንችስተር ሲቲ በ44 ይከተላል፣ ቶተንሃም ሶስተኛ በ42፣ ቼልሲ እና አርሰናል በተመሳሳይ 37 ነጥብ አራተኛና አምስተኛ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ በ29 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡