loading
የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ማሻሻል የሚያስችል መርሃ ግብር ተጀመረ

አርትስ 16/04/11

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያስችል ብሄራዊ መርሃ ግብር አስጀመሩ።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ የስራ ፈጠራ መርሃ ግብር አካል ሲሆን፥ ንግድን በመጀመርናበማሳደግ ኢትዮጵያ ያላትን ተወዳዳሪነት ይጨምራል ተብሏል።

ብሄራዊ መርሃ ግብሩ በ10 አስፈፃሚ ተቋማት የሚተገበሩ 80 ልዩ ተግባራትንም ይዟል።

መርሃ ግብሩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቆጣጣሪነት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፖሊሲና አፈፃፀም ክፍል ክትትል እየተደረገበት፥ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትኮሚሽን አስተባባሪነት የሚተገበር ይሆናል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ በማደግ ላይ ያለ እና ጠንካራ የግል ዘርፍ ለሥራ ፈጠራ አጀንዳ ወሳኝ መሆኑ ተነስቷል።

መንግስትም የግሉን ዘርፍ እድገት የሚገቱና የሥራ ዕድል እንዳይፈጥር የሚያግዱ እንቅፋቶችን ለይቶ በማውጣት ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ነውየተባለው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *