loading
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋርም ተገናኝተው ተወያይተዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

የቻይና የሀገር ውስጥ ጉዳዮች አማካሪና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት ነው በኢትዮጵያ የጀመሩት።

ዋንግ ዪ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ቡርኪናፋሶ፣ ጋምቢያና ሴኔጋል ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን፥ ጉብኝቱ የአፍሪካና ቻይና ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *