loading
በሀገራችን የገበያ መረጃ ልውውጥ ስረዓቱ ያልዘመነ እና ተደራሽነት የሌለው ነው ተባለ

በሀገራችን የገበያ መረጃ ልውውጥ ስረዓቱ ያልዘመነ እና ተደራሽነት የሌለው ነው ተባለ

ይህ የተባለው የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አዲስ  የገበያ መረጃ  መተግበሪያ ሶፍት ዌር ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

የህብረት ስራ ማህበር ኤጀንሲው  ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር ለአርትስ እንደተናገሩት   በሀገራችን የገበያ መረጃ ልውውጥ ስረዓቱ ያልዘመነ እና ተደራሽነት የሌለው መሆኑ በአምራቾች፣ ሸማቾች እና ተጠቃሚዮች መካከል ውጤታማ ትስስር  እንዳይኖር አድርጎታል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ኡስማን ገለፃ በዚህም ምክንያት ነው ይህንን የገበያ መረጃ መለዋወጫ መተግበሪያ ሶፍትዌር ዲዛይን ማድረግ ያስፈለገው፡፡

በዚህ መተግበሪያ አርሶአደሮች በዋናነት ተጠቃሚ ቢሆኑም የንግዱን ዘርፍ በአጠቃላይ ውጤታማ እንደሚያደርግ  ነው ዳይሬክተሩ የነገሩን፡፡

ሶፍትዌሩ ከአለም አቀፍ ገበያ ተሞክሮ የተወሰደ ቢሆንም ማህበረሰቡን ያገናዘበ ነውም ተብሏል፡፡

በሀገራችን ያለውን የግብይት መረጃ ስረዓት ያዘምናል የተባለው ይህ መተግበሪያ እንደ ሙከራ  በ3 ክልሎች እና 40 የህብረት ስራ ማህበራት ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሰምተናል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *