loading
ፋሲል ከነማ ጎንደር ላይ ደደቢትን ድል አድርጓል

ፋሲል ከነማ ጎንደር ላይ ደደቢትን ድል አድርጓል

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት ተስተካካይ ግጥሚያ በፋሲል ከነማ እና ደደቢት መካከል በፋሲለደስ ስታዲየም ተካሂዶ አፄዎቹ የ2 ለ 1 ድል ተቀዳጅተዋል፡፡

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club

ለጎንደሩ ቡድን የድል ግቦችን ሙጂብ ቃሲም እና ኤዲ ቤንጃሚን በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ሲያስቆጥሩ፤ ለእንግዳው ደደቢት ደግሞ ብቸኛዋን ጎል እንዳለ ከበደ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

ይህን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ15 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ፤ ደደቢት በ3 ነጥብ እና 10 የግብ ዕዳ የደረጃ ሰንጠራዡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል፡፡

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *