የዛሬ ውሎ የተጫዋቾች ዝውውር የጭምጭምታ ወሬዎች
የትኛው ክለብ ማንን ለመቅጠር ፈለገ ?
የማንችስተር ዩናይትዱ ማሩዋን ፌላኒ በ15 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ፤ ስሙ ከኤሲ ሚላን፣ ፖርቶ እና የቻይናው ጓንጉዙ ኤቨርግራንዴ ጋር ተያይዟል፡፡ ሚረር
…………………………….
ቼልሲ በውሰት ውል በኤሲ ሚላን እየተጫወተ ያለውን የዩቬንቱስ ንብረት፤ የ31 አመት አጥቂ ጎንዛሎ ሂግዌን በዚህ ሳምንት ማብቂያ ሙሉ ፊርማውን ያጠናቅቃል ተብሏል፡፡ ቴሌግራፍ
………………………………
የኤሲ ሚላን አሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ ግን ጎንዛሎ ሄግዌን ክለቡን እንደሚለቅ አላሳወቀኝም ብሏል፡፡ ኢቭኒንግ ስታንዳርድ
……………………………
የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ኪኮ ካሲያ በሊድስ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ወደ እንግሊዝ በመብረሩ ከማክሰኞ ዕለት ልምምድ መፎረፉ ተነግሯል፡፡ አስ
…………………………….
ክሪስቲያን ኢሪክሰን በቶተንሃም የቀረበለትን አዲስ ውል የመፈረም ፍላጎት የለውም ተብሏል፤ ሪያል ማድሪድ ደግሞ የዴንማርካዊው አማካይ ቀጣዩ የተጫዋቹ ማረፊያ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አስ
………………………………
አርሰናል ቤልጅየማዊውን የክንፍ መስመር ያኒክ ካራስኮ የማስፈረም ፍላጎት ቢኖራቸውም፤ የ30 ዓመቱን ጀርመናዊ አማካይ ሜሱት ኦዚል ካልሸጡት በስተቀር ካራስኮን ለማስፈረም ለቻይናው ዳሊያን ይፋንግ ጥያቄ አያቀርቡም ተብሏል፡፡ ፎክስ ስፖርትስ ኤሲያ