loading
ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ አዋጅን አፀደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ አዋጅን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ 19 መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን፥ በውይይቱ በቀረቡለት ሁለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

በዚህም ምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህና ዴሞከራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል።

ረቂቅ አዋጁ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች በስደተኞች ጉዳይ ላይ የተቀበለቻቸውን ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

የምክር ቤቱ አባላትም በስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅ ከተወያዩ በኋላ፤ አዋጁን ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቀውታል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመንግስትና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አፖርቹኒት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የተደረገውን 83 ነጥብ 3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ጥያቄ እና አስተያየት ካቀረቡ በኋላ፤ ረቂቅ አዋጁን በአብላጫ ድምጽ አጽቀውታል፣                                                                        ዘገባው የኤፍ.ቢ.ሲ ነው።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *