loading
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ  ሁለተኛ የልማት አጋር ውይይታቸውን የግብርና ልማት አለም አቀፍ ፈንድ ፕሬዝዳንት ጊልበርት ሆዉንግቦ ጋር አካሂደዋል፡፡

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ  ሁለተኛ የልማት አጋር ውይይታቸውን የግብርና ልማት አለም አቀፍ ፈንድ ፕሬዝዳንት ጊልበርት ሆዉንግቦ ጋር አካሂደዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ጠ/ሚር ዐቢይ ባለፉት ጥቂት ወራት በአገሪቱ የተመዘገቡትን ለውጦች ለማምጣት ያሳዩትን ቆራጥነት አድንቀዋል::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው የመስኖና የምግብ ዋስትና እንቅስቃሴዎችን ማጠናከር ላይ አተኩረዋል::

የግብርና ልማት አለም አቀፍ ፈንድ ለኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ ከአፍሪካ ትልቁ ሲሆን በመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በተለይም በአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ምርታማነት ላይ መሰረት ያደረገ ነው:: ሁለቱ ወገኖችም እገዛ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎት ለማሟላት በመካከለኛ ደረጃ የመስኖና የገጠር ፋይናንስ ፍሰትን ለማጠናከር ተስማምተዋል::

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *