ሪያል ማድሪድ የእንግሊዙን ማንችስተር ዩናይትድ በመብለጥ የዓለማችን ሀብታም ክለብ ተሰኝቷል
ሪያል ማድሪድ የእንግሊዙን ማንችስተር ዩናይትድ በመብለጥ የዓለማችን ሀብታም ክለብ ተሰኝቷል
ከእግር ኳስ ጋር የተገናኙ የፋይናንሽያል እንቅስቃሴ መረጃዎች ይፋ የሚያደርገው ዳሎይቴ፤ የዓለም 20 ሀብታም ክለቦችን ዝርዝር ይፋ ባደረገው ሪፖርት፤ የስፔኑ ሪያል ማድሪድ ክለብ 674.6 ሚሊየን ፓውንድ ገቢ ወደ ካዝናው በማስገባት ማ/ዩናይትድን መብለጡን አስታውቋል፡፡
ዩናይትድ ከነበረበት የቀዳሚነት ደረጃ በዚህ ሪፖርት ወደ ሶስተኛ ደረጃ የወረደ ሲሆን ሌላኛው የስፔን ቡድን ባርሴሎና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በFootball Money League (የእግር ኳስ የገንዘብ ሊግ) የደረጃ ሰንጠራዥ በ2017/18 የውድድር ዓመት እንደሚያሳየው የ20 ሀብታም ክለቦች የገቢ ሀብት መጠን ክብረወሰን በሆነ ደረጃ ወደ 6 በመቶ የተመነደገ ሲሆን 7.4 ቢሊዬን ደርሷል ተብሏል፡፡
ስድስት የእንግሊዝ ክለቦች ደግሞ በመጀመሪያው 10 ደረጃዎች ውስጥ ተካትተዋል፡፡
የሀብት መጠን የማሳወቁ መንገድ ይህ 22ኛው ሲሆን ክለቦች የሚያስገቡትን ገቢ ብቻ እንጂ ዕዳቸውን አይጨምርም ተብሏል፡፡
በዚህ ዓመት ይፋ በሆነው ሪፖርት በቀዳሚው ሪያል ማድሪድ እና በተከታዩ ባርሴሎና መካከል ያለው የገንዘብ ልዩነት የ60.5 ሚሊየን ዩሮ ነው፡፡
ለሎስ ብላንኮስ የገቢ መጠን ከፍ ማለት በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ሊቨርፑል ድል ማድረጉ ሲጠቀስ የዳሎይቴን የገንዘብ ሊግ ደረጃ ለ12 ጊዜ ያህል በመቆናጠጥ ይመራል፡፡
የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ እና ማንችስተር ሲቲ እስከ አምስት ባለው ደረጃ ውስጥ ሲገኙ፤ ፒ.ኤስ ጂ፣ ሊቨርፑል፣ ቼልሲ፣ አርሰናል እና ቶተንሃም ሆትስፐር ደግሞ ከስድስት እስከ አስር ባለው ደረጃ ላይ የተቀመጡ ቡድኖች ናቸው፡፡