loading
አባይ ኢንዱስትሪያል ልማት ማህበር ደጀን ከተማ ላይ የሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት የውል ስምምነት ተፈራረመ::

አባይ ኢንዱስትሪያል ልማት ማህበር ደጀን ከተማ ላይ የሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት የውል ስምምነት ተፈራረመ::

የውል ስምምነቱ ሥነ ስርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የአባይ ኢንዱስትሪያል የልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መላኩ አለበል ተገኝተዋል ሲል አመራ መገናኛ ብዙሃን ደርጀት ገልፃôል። ።

ፋብሪካው በ8 ነጥብ ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባ ሲሆን፥ በ24 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ታዉቋል።

በቀን 5 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንደሚያመርት የተገለጸ ሲሆን፥ ለ665 ሰዎች ቋሚ የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት  እንዳገኘነዉ መረጃ  ፋብሪካዉ  በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም የሰራተኞቹን ቁጥር ወደ 1 ሺህ ከፍ እንደሚያደርግ ነው የተጠቆመው።

የልማት ማህበሩ ሥምምነቱን የተፈራረመው ከቻይናው ኤች ዋይ እና ከዴንማርኩ ኤፍ ኤል ኤፍ ኩባንያዎች ጋር ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *