loading
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግጭት ለመፍጠር ተልዕኮ ይዘው ሲሰሩ የነበሩ ከ150 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግጭት ለመፍጠር ተልዕኮ ይዘው ሲሰሩ የነበሩ ከ150 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግጭት ለመፍጠር ተልዕኮ ይዘው ሲሰሩ የነበሩ ከ150 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ለሕግ ማቅረቡን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም እንዳሉት የፖለቲካ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን በማወክ ግጭት እንዲቀሰቀስ ሲሰሩ እንደነበር የተጠረጠሩ ከ150 በላይ መምህራንና ተማሪዎችን በመለየት ለሕግ ቀርበዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን በተመለከተ ውይይት አድርጓዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሰላሌ፣ እንጂባራና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ በምልከታውም የውኃና የመብራት ችግር፣ የግንባታ መጓተትና በግንባታ ጥራት ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩ በዩኒቨርሲቲዎቹ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲታወክ ምክንያት መሆናቸውን ገምግሟል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወሰን ማካለል ችግር፣ የመሠረተ ልማትና የግብዓት ችግር፣ የተለያዩ የትምህርት መሣሪያዎች ግዥ መጓተት በመማር ማስተማሩ ላይ ችግር እየፈጠሩ መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው መታዘቡንም ገልጿል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *