በኢትዮጵያ የግብር አከፋፈል ፖሊሲው እና የፖለቲካ ስርአት ኢንቨስትመንት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ተባለ
በኢትዮጵያ የግብር አከፋፈል ፖሊሲው እና የፖለቲካ ስርአት ኢንቨስትመንት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ተባለ
ይህ የተባለው አፍሮ ግሎባል ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፣ከገቢዋች ሚኒስትር እና ሌሎችም ተቋማት ጋር በመሆን የግብር አሰባሰብ ፖሊሲ እና ህግ እንዲሁም የፖለቲካ ስረአት ኢንቨስትምንትን ያለው ሚና፣ ችግሮቹ እና መፍትሄዎቹ በሚል በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
ግብር እና ኢንቨስትመንት ትልቅ ቁርኝት እንዳላቸው እና በሀገራችን የግብር አከፋፈል ፖሊሲው እና የፖለቲካ ስርአቱ ኢንቨስትመንት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በውይይቱ ተጠቅሷል፡፡
የግብር አሰባሰብ ፖሊሲዎች እና ህጎች ማሻሻያ በጥናት የተደገፈ አለመሆኑ፣ በመንግስት እና በግብር ከፋዩ ማህበረሰብ መካከል ያለው ክፍተት፣ የህግ እና የፖሊሲ አፈፃፀም ክፍተት እና ሙስና በግብር አከፋፈል ስርአቱ እንደክፍተት የተነሱ ሀሳቦች ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ እና አስተዳደር ትምህርት ክፍል ዲን ዶክተር ሰለሞን ንጉሴ የሀገሪቱ የፖለቲካ መዋቅርም በሀገሪቱ የግብር አሰባሰብ ስርአቱ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡