loading
የፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ዙፋን አሁንም እየተነቃነቀ ነው

የፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ዙፋን አሁንም እየተነቃነቀ ነው፡፡

በሱዳን በወባ ሳቢያ የተቀሰቀሰው ቁጣ መልኩን ቀይሮ የአስተዳደር ለውጥ  አጀንዳ ከሆነ ከወር በላይ አስቆጥሯል፡፡

ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ የሚወጡ ሰዎች እና የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ በመግባታቸው እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 29 ከፍ ማለቱም ተሰምቷል፡፡

ነገር ግን ይህን ያሉት በመንግስት በኩል ተወክለው ነገሩን አጣራን ያሉት አካላት ናቸው እንጂ ገለልተኛ ነን የሚሉ ወገኖች ቁጥሩን ወደ 40 ያስጠጉታል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት አልበሽር ሰሞኑን ወደ ኳታር ተጉዘው ባቀረቡት ጥያቄ ከዶሀ መንግስት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን በካርቱም እና በበርካታ የሱዳን ከተሞች እየተባባሰ የመጣው አመፅ መልኩን ቀይሮ አልበሽር ከስልጣናቸው ይውረዱ የሚል በመሆኑ ከዚህ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ቢደረግም የረፈደበት መፍትሄ ነው ተብሏል፡፡

አልበሽር እና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ስልጣን ማስተላለፍ የሚቻለው በምርጫ ብቻ ነው  ከዚህ ውጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ህገ ወጥ ነው ቢሉም ሰሚ ጆሮ ግን አላገኙም፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *