loading
አሜሪካ ኢራቅን በወረረችበት  ጦርንት አሸናፊዋ ኢራን  መሆንዋን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

አሜሪካ ኢራቅን በወረረችበት  ጦርንት አሸናፊዋ ኢራን  መሆንዋን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

በ2016 የተጠናቀቀዉና ዘግየት ቢልም  አሁን ይፋ የተደረገዉ ጥናት አሜሪካ ኢራቅ ላይ ባዘመተችዉ ጦር ተጠቃሚዋ ኢራን ብቻ መሆንዋን ገልጿል ፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር አናዶሉ ኤጀንሲን ጠቅሶ እንደዘገበዉ  ሁለት ጥራዝ ያለዉና በአነድ ሺህ ሶስት መቶ ገጽ የቀረበዉ ጥናት  በኢራቅ ጦርነት ዉስጥ የነበሩ ስህተቶችና ስኬቶችን በዝርዝር የያዘ ነዉ፡፡

ጥናቱ በ2013 በቀድሞ የመከላከያ አዛዥ ጀነራል ሬይ ኦዴርኖ የተጀመረ ሲሆን አሁን ባሉት በጀነራል ማርክ ሜሪሊ የቀረበ ነዉ ተብሏል፡፡

በጥናቱ  አሜሪካ በ2003 ኢራቅን ከወረረችበት ጀምሮ ጦርዋን ማስወጣት እስከጀመረችበት ድረስ የተከሰቱ ሁነቶችን ያያዘ ሲሆን ፤የዳይሽ ሽብርተኞች ማንሰራራትን ጨምሮ  የሶርያንና የኢራንን አካባያዊ ተጽእኖ ያካተተ ነዉ ተብሏል፡፡

በዚህ ጥናት ያላታሰበዉና የተገኘዉ ዉጤት  ግን ጦርነቱ ድል ያስገኘዉ ለኢራን ብቻ መሆኑን ሚያመለክት ሲሆን ይህም ሁኔታ ለኢራን  በአካባቢዉ ተጽእኖ እንድታሳርፍ እድል ፈጥሮላታል ተብሏል፡፡

አሁን በኢራቅ የኢራን ብሮድካስት ሚዲያ ተመራጭ ነዉ፤የኢራቅ ሱፐር ማርኬቶችም የሚይዙት የኢራንን ወተት ቅቤና ዶሮ ሆንዋል ፤ይህም ታዲያ በኢራቅ አለመረጋጋትና መዳከም ለኢራን የተፈጠረ ያላታሰበ ሲሳይ ሆንዎላታል፡፡

ጥናቱ ባጠቃላይ አሜሪካ ጦርዋን ወደ ኢራቅ ማስገባትዋ ለእሷ ኪሳራ መሆኑንን  ለተቀናቃኝዎችዋ ግን ድል ነዉ ሲል ደምድሟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *