loading
በኦነግና መንግስት መካከል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተቋቋመው የዕርቅ ኮሚቴ ለእርቁ ስኬታማነት እየሰራ መሆኑን አሳወቀ

በኦነግና መንግስት መካከል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተቋቋመው የዕርቅ ኮሚቴ ለእርቁ ስኬታማነት እየሰራ መሆኑን አሳወቀ። ከሁለቱም ወገን በኩል ለእርቁ ያለውን ተነሳሽነትም አድንቋል።

የኮሚቴው ተወካዮች ትላንት በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ከሆነ የዕርቁን ሂደት በአባ ገዳዎችና በተቋቋመው ኮሚቴ ለማስኬድ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡

የቴክኒክ ኮሚቴውን በወከል ለሚዲያዎች ማብራሪያ የሰጡት ተወካዮች አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጀዋር መሃመድ ሲሆኑ ሂደቱን ለማፋጠን ከሁለቱም ወገን እርቁን እውን ለማድረግ ያለውን ተነሳሽነትና ዝግጁነት በበጎ ጎኑ እንደሚያዩት ገልፀዋል።

በቀጣይ ቀናት የኦነግ የጦር ሰራዊት ወደተዘጋጀለት ካምፕ እንዲገባ ለማድረግ ኮሚቴው ጦሩ ወዳለበት ቦታ እንደሚንቀሳቀስ አሳውቀዋል፡፡

የኮሚቴው ተወካዮች እንዳሉት ለጦሩ አቀባበል የሚደረግበትንና ለማረፊያነት የተዘጋጁትን ስምንት ስፍራዎችንም ኮሚቴው ቀድመው ይጎበኛሉ። ኮሚቴው ከቻለ ከተቻለ ጦሩን ወደተዘጋጀለት ካምፕ የማስገባቱ ስራ ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ እንዲሰራ መታቀዱንም ተናግረዋል።

አሁንም ቢሆን በመንግስትም ሆነ በኦነግ በኩል የሚነሱ ቅሬታዎች ቢኖሩም የአባ ገዳዎችን ትዕዛዝ ማክበር አስፈላጊ ነው ብለዋል የኮሚቴው ተወካዮች ። የችግሮቹን ዝርዝር ግን ለመገናኛ ብዙሃን ለማሳወቅ አልፈቀዱም፡፡

 

 

 

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *