loading
በአዲሱ የስራ ድልድል አንድም ሰራተኛ እንደማይቀነስ የኦሮሚያ ክልል የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

በአዲሱ የስራ ድልድል አንድም ሰራተኛ እንደማይቀነስ የኦሮሚያ ክልል የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

አዲሱ የስራ ድልድልም አስከ ጥር 30 2011 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች አዲስ የስራ ምደባ  እየተካሄደ መሆኑን ተከትሎ የቢሮው ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪ በሰጡት መግለጫ በክልሉ በሚደረገዉ የሰራተኛ ድልድል ሰራተኛ የሚቀነስበት ሂደት የለም ብለዋል፡፡

እንደ ሀላፊው ገለፃ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ ያላቸውን አቅም፣ እውቀት እና ስነ ምግባር መሰረት አድርጎ ነው እየተካሄደ ያለው ፡፡

በአዲስ መልክ በተዋቀሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥም ሁሉም ሰራተኞች በሚመጥናቸው ስራ ዘርፍ ላይ ተወዳድረው እንዲመደቡ እየተደረገ በመሆኑ በአዲሱ የስራ ድልድል አንድም ሰራተኛ የመቀነስ ስጋት እንዳያድርበት ገልፀዋል።

በተጨማሪም አዲሱ አደረጃጀት በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እቅድ ተይዞበት እየተሰራ ነው ብለዋል ሀላፊው።

አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ እስከ ጥር 30 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተነግሯል።

ከኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ እንዳገኘነዉ መረጃ የመንግስት እና የህዝብን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎትን  እንዲያገኝ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *