loading
ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች የ2018/19 የፊፋ ባጃቸውን ተረከቡ

ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች የ2018/19 የፊፋ ባጃቸውን ተረከቡ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ዝግጅት፤ ከአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የተላከላቸውን የ2018/19 የፊፋ ባጅ ተቀብለዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአርትስ በላከው መረጃ፤ የፊፋ ባጁን የተረከቡት ሰባት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኞች እንዲሁም ሰባት ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞች ሲሆኑ በድምሩ 14 ወንድ ኢንተርናሽናል ዳኞች ዕውቅናን አግኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አራት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኞች እንዲሁም አራት ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞች በድምሩ ስምንት ሴት ኢንተርናሽናል ዳኞች በአጠቃላይ ሀያ ሁለት ኢንተርናሽናል ዳኞች የፊፋ ባጅ ተቀብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አሊሚራ መሃመድ እጅ ከአለም አቀፉ እግር ኳስ ማሀበር (ፊፋ) የተላከውን የፊፋ ባጅ ለአርቢትሮቹ አስርክበዋል ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *