የህክምና ጥራትን ማሻሻል የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳድግ ያግዛል ተባለ፡፡
የህክምና ጥራትን ማሻሻል የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳድግ ያግዛል ተባለ፡፡
ይህ የተባለዉ የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር
በሀገር ውስጥ የሚገኙ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካዎች የሚጠናከሩበትን መንገድ በመከሩበት ወቅት ነዉ፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን እንዳሉት የሀገራችንን የህክምና ጥራት በማሻሻል ኢኮኖሚ ያችንን ማሳደግ ይቻላል ፡፡
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 በተደረገ ጥናት ኢትዮጵያ የህክምና መድኀኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት 474 ሚሊዮን ዶላር አውጥታለች ተብሏል::
በሀገር ውስጥ የሚገኙ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካዎች ከተጠናከሩ ግን ሀገሪቱ ለህክምና መሳሪዎችና መድሀኒት ግዢ የምታወጣዉን ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሪ ማስቀረት ያስችላል ፡፡