ትንናት ምሽት የተደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡
ትንናት ምሽት የተደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ቡድኖች ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ሁለት ግጥሚያዎች በተመሳሳይ ሰዓት ተካሂደዋል፡፡
እንግሊዝ ምድር ላይ የጀርመኑን ባየር ሙኒክ ያስተናገደው የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል ጨዋታውን ያለግብ በአቻ ውጤት አጠናቅቋል፡፡
ባለሜዳዎቹ ቀያዮቹ በርካታ የግብ አጋጣሚዎችን ማግኘት ቢችሉም ማኔ፣ ሳላህ፣ ማቲፕ እና ሌሎች ወደጎልነት መቀየር ተስኗቸዋል፡፡ ሙኒክ በግናብሪና ኮማን አማካኝነት ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል በተደጋጋሚ በመሄድ እንቅስቃሴ ያደረጉ ቢሆንም ፍሬ ግን ማፍራት አልቻለም፡፡
የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ቀያዮቹ በመልሱ የአሊያንዝ አሬና ፍልሚያ ማሸነፍ አሊያ ግብ የተቆጠረበት የአቻ ውጤት በቀጥታ ወደ ሩብ ፍፃሜው እንዲሻገር ሲያግዘው፤ የባቫርያኑ ቡድን ማሸነፍ ግዴታው ሁኗል፡፡
ፈረንሳይ ግሮፓማ ስታዲየም ላይ ኦሊምፒክ ሊዮን እና ባርሴሎና ተገናኝተው በተመሳሳይ ያለግብ 0 ለ 0 በሆነ የአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ባርሳ በምሽቱ ተጭኖ የተጫወተ ሲሆን በሙሉ ግጥሚያው 25 ያህል ሙከራዎችን አድርጎ አንዱንም ወደ ግብነት መቀየር አልቻለም፡፡ ሊዮኖች ጥቂት የሚባሉ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ሳይሳካላቸው ቀርቶ፤ በሜዳቸው የቤት ስራቸውን ሳይከውኑ ወጥተዋል፡፡ የመልሱ ግጥሚያ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ካምፕ ኑ ላይ ይደረጋል፡፡