loading
ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባጅፋር እና መከላከያ ይጫወታሉ፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባጅፋር እና መከላከያ ይጫወታሉ፡፡

የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መጠናቀቅን ተከትሎ፤ በዙሩ በተለያየ ምክያቶች ያልተካሄዱ የሊጉ ግጥሚያዎች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡

በዛሬው ዕለት ክልል ስታዲየም ላይ አንድ ጨዋታ ሲደረግ፤ ዘንድሮ በአፍሪካ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ሲወዳደሩ የነበሩት ጅማ አባ ጅፋር እና መከላከያ ቀን 9፡00 ሲል ጅማ ስታዲየም ላይ ይፋለማሉ፡፡

ከተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ እና አስተዳደራዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ በመጠኑም ቢሆን ያለበትን ውዝግብ እየፈታ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር ከድል መልስ ጨዋታውን ያደርጋል፤ ክለቡ በቅርቡ ከኤልያስ ማሞ ጋር በስምምነት መለያየቱም ይታወሳል፡፡

የጦሩ በድን በሰፊ የግብ ልዩነት ሽንፈት በኋላ ወደ ድል የተመለሰ ሲሆን ጅማ ላይ ሁለቱም ቡድኖች ከወራጅ ቀጠናው በደንብ ለመራቅ ሲሉ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች ባደረጓቸው ጨዋታዎች በተመሳሳይ 17 ነጥቦችን በመያዝ በተሸከሙት የግብ ዕዳ ተበላልጠው 10ኛ እና 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በነገው ዕለት ደግሞ ሲዳማ ቡና ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ አምርቶ ድሬዳዋ ከነማን ይገጥማል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠራዥን መቐለ 70 እንደርታ በ32 ነጥብ ሲመራ፣ ሲዳማ ቡና በ27 ሁለተኛ ነው፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ነጥብ ሶስተኛ ፤ ሀዋሳ እና ፋሲል ከነማ በእኩል 24 ነጥቦች አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጥዋል፡፡

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ አና ደደቢት ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ናቸው፡፡

የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ11 ጎሎች ይመራል፤ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቐለ በ10 ጎሎች ይከተላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *