ታይዋን ዲሞክራሲን የሚጋፋ ስምምነት አልፈፅምም አለች፡፡
ታይዋን ዲሞክራሲን የሚጋፋ ስምምነት አልፈፅምም አለች፡፡
የታይዋኗ ፕሬዝዳንት ፃይ ኢንግ ዌን ከየትኛውም አካል የሚመጣ ጥያቄ ዲሞክራሲን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ በምንም መልኩ አንቀበለውም ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቷ ይህን ያሉት ለቻይና ጥሩ አመለካከት አለው የሚባለው ፓርቲ መጭውን ምርጫ ካሸነፍኩ ከቤጂንግ ጋር ስምምነት የማድረግ ሀሳብ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡
ዌንግ የታይዋንን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የትኛውም ስምምነት ተቀባይነት የለውም ብቻ ሳይሆን አጥብቀን የምንቃወመው መሆኑ ይታወቅልን ነው ያሉት፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው በፕሬዝዳንት ፃይ ኢንግ ዌን የሚመራው ዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2020 በሚደረገው ምርጫ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡
ቻይና ታይዋንን በሀይል ወደ ራሴ ግዛት አጠቃልላለሁ የሚለውን ዛቻ ካላቆመች በቤጂንግ እና በታይዋን መካከል ትክክለኛ ሰላም ይሰፍናል ብሎ መጠበቅ አይቻልም ብለዋል ፕሬዝዳንቷ፡፡
ቻይና ግን አሁንም ታይዋን የአንዲት ቻይና አካል እንጂ ራሷን ችላ እንደ ሀገር መቀጠል የለባትም በሚለው አቋማ እንደፀናች ናት፡፡
መንገሻ ዓለሙ