ሉሲ የሰላም ጉዞዋን ከትዉልድ ቀየዋ አፋር ክልል ልትጀምር ነዉ፡፡
ሉሲ የሰላም ጉዞዋን ከትዉልድ ቀየዋ አፋር ክልል ልትጀምር ነዉ፡፡
ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር የሽኝት መርሃ ግብር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተካሄዷል፡፡
የሽኝት መርሃ ግብሩ “ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” በሚል መሪ ቃል “የሰው ዘር እናት” የተሰኘችዋን የድንቅነሽን ቅሪተ አካል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎችና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚደረገውን ጉዞ ማስጀመሪያ ነው።
ሽኝቱ ላይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የሀይማኖት አባቶችና የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተገኝተዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ባስተላለፉት መልእክት፥ የጉዞ ሉሲ ዋነኛው ዓላማ አንድነታችንን እና አብሮነታችንን ማጠናከር ነው ብለዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው፥ “የጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር እኛን እርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ከዓለም ጋር የሚያስተሳስር ነው” ብለዋል።
ሉሲ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን ዓለምን ከኢትዮጵያ ጋር የምታስተሳስር ገመድ ነች ያሉት ዶክተር ሂሩት፥ ይህንን ገመድ በመጠቀም በጉዙ ሉሲ በአንድነታችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
የጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር የድንቅነሽን ቅሪተ አካል ድሬዳዋን ጨምሮ በዘጠኙም ክልሎች በመዘዋወር በማስጎብኘት ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን እንደሚሰበክበት ተነግሯል።
የሉሲ ጉዞ በአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ማለትም በኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ሪፐብሊክ እንዲሁም ኬንያና ኡጋንዳ የሚካሄድ እንደሆነም ታውቋል።